Digital Security Guideline – Amharic

የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ጋዜጠኞች ሃሳባቸውን በነፃነት በመግለፃቸውና ለአላማቸው በመቆማቸው በባለስልጣነት ኢላማ ውስጥ ሲገቡ ነበር። ብዙ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት አፋኝ መንግስታት በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ የሳይበር ደህንነት ሰባሪ ካምፓኒዎች (hacking companies) በመቅጠር የሰብኣዊ መብት ተሟጋቾችንና ጋዜጠኞችን ያጠቃሉ። ከነዛ አገራት መካከልም ኢትዮጵያ አንዷ ናት። ይህ የዲጂታል ደህንነት መመሪያ በኢትዮጵያ የሚገኙ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾችንና ጋዜጠኘችን የኦንላይን እንግስቃሴ ደህንነት ክህሎት እንዲያዳብሩ በአማርኛ፤ ኦሮምኛ እና እንግሊዝኛ የተሰናዳ ነው።